አህባሽo P

አህባሽ

አህባሽ የሚባለው አንጃ ከውጪ ሲታይ የሚከተሉት ገጽታዎች አሉት፡፡

1. “አህባሽ” የኢትዮጵያ ተወላጅ በነበሩት ሼኽ አብዱላሂ ሙሐመድ ዩሱፍ (ወይም ሼኽ አብዱላህ አል-ሐረሪ አል-ሐበሺ) ጠንሳሽነት በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ውስጥ በ1983 ዓ.ል. የተመሰረተ ፖለቲካና ሀይማኖትን አንድ ላይ አጣምሮ የሚራመድ አንጃ (ጀመዓ) ነው፡፡

2. አንጃው በአረብኛ አጠራር “ጀምኢያቱል መሻሪኢል ኼይሪያቱል ኢስላሚያ” ይባላል፡፡ የእንግሊዝኛ ስሙ “Association of Islamic Charitable Projects” የሚል ነው፡፡

3. “አህባሽ” የአንጃው ተከታዮች በጋራ የሚጠሩበት የቡድን ስማቸው ነው፡፡ እያንዳንዱ የጀመዓው አባል “ሀበሺይ” ይባላል (ሴት ከሆነች “ሀበሺያ” ትባላለች)፡፡ በሀገራችን ውስጥ ያሉት የአንጃው ተከታዮች ግን “አህባሽ” ከሚለው ስም ይልቅ “የሼኽ ጀመዓ ነኝ” ማለትን ይመርጣሉ፡፡

4. “አህባሽ” የሚለው ቃል ምንጩ “ሐበሻ” የሚለው የሀገራችን የዐረብኛ ስም ነው፡፡ ይህም የአንጃው መስራች የተወለዱበትን ሀገር (ኢትዮጵያን) ያመለክታል፡፡ የጀመኣው አባላት ይህንን ስም ይወዱታል እንጂ አይቃወሙትም፡፡ ስለዚህ እኛ የአህባሽ ተቃዋሚዎች ያወጣንላቸው ስም አድርጋችሁ እንዳታዩት ያስፈልጋል፡፡ (እውነቱን ለማወቅ አህባሾችን ራሳቸውን ጠይቋቸው፡፡ ዌብሳይቶቻቸውንና የፌስቡክ ቡድኖቻቸውን የሚጠሩበትንም ስም ተመልከቱ)፡፡

5. አንጃው በሄደበት ሀገር ሁሉ “መንግስታዊ ያልሆነ ማህበር” ተብሎ ነው የተመዘገበው፡፡ በመሆኑም ማህበራዊ አገልግሎት የሚሰጡ አንዳንድ ተቋማትን (እንደ መድረሳና የጤና ክሊኒክ የመሳሰሉትን) ከፍቷል፡፡ በሀገራችን ውስጥ ግን እንዲህ አይነት ፕሮጀክቶችን የሰራ አይመስለኝም፡፡

6. አህባሽን የመሰረቱት “ሼይኽ አብዱላህ አል- ሀረሪ” ከሶስት አመታት በፊት ቢሞቱም እስካሁን ድረስ የአንጃው ከፍተኛ መንፈሳዊ መሪ ተደርገው ይታያሉ፡፡ በመሆኑም የጀመዓው አባላት “ሼይኹና” ወይም “ሰይዱና” ይሏቸዋል፡፡ በቤታቸው ግድግዳና በሌሎችም ቦታዎች (በሞባይል ስልካቸውም ጭምር) የመሪያቸውን ፎቶ ያስቀምጣሉ፡፡

7. የአንጃው ዋና ማዕከል (Head Quarter) ያለው በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤይሩት ውስጥ ነው፡፡ በተጨማሪም በሶሪያ፣ ዮርዳኖስ፣ ግብጽ፣ አሜሪካ፣ እንግሊዝ፣ ካናዳ፣ ጀርመን፣ ዴንማርክ፣ አውስትራሊያ ወዘተ… ቅርንጫፎች አሉት፡፡

8. የአህባሽ በርካታ ተከታዮች ያሉትም እዚያው በሊባኖስ ሀገር ሲሆን አንጃው በአሜሪካ፣ ካናዳና አውስትራሊያም ጠንካራ ጀመዓ እንደመሰረተ ይታወቃል፡፡ ወደ ሀገራችን ከገባ ከአስር ዓመታት በላይ ቢሆነውም ብዙ ተከታዮችን መመልመል አልቻለም፡፡ (አብዛኛው ህዝብ አንጃው እዚህ መኖሩን እንኳ አያውቅም)፡፡

9. አንጃው የሻፊዒይ መዝሀብ ተከታይ ነኝ ይላል፡፡ የዓቂዳ ትምህርቱም “አሽዐሪ” (ኢማም አቡል ሐሰን አል-አሽዐሪ ያስተማሩት መንገድ) እንደሆነ ያወሳል፡፡ የ“ሪፋዒያ” የሱፊ ጠሪቃ ተከታይ እንደሆነም ይገልጻል፡፡

10. አንጃው ስብከቱን ለተከታዮቹ የሚያስተምርበት “መርከዝ” (ማእከል) አለው፡፡ በየመርከዙ የሚቀመጡ ሼይኾችንም በቤይሩት እያሰለጠነ በዓለም ዙሪያ ያሰራጫል፡፡ በመርከዙ ተምረው የሚወጡ ጎበዝ ተማሪዎችም ቤይሩት ሄደው የሚማሩበት የከፍተኛ ትምህርት እድል (scholarship) ይሰጣቸዋል፡፡

11. የአንጃው መንፈሳዊ ትምህርቶች በአብዛኛው የሚያተኩሩት በአቂዳ፤ “ፊቅህ” እና “ተሰውፍ” (Sufism) ላይ ነው፡፡ የትምህርት ቋንቋውም አረብኛ ነው፡፡

12. አንጃው ተከታዮቹን ከሚያስተምርባቸው የመማሪያ መጽሀፍት መካከል በስፋት የሚታወቁት ሁለት ናቸው፡፡

12.1 “ሙኽተሰር አብዱላህ አል-ሐረሪ”

a) ይህ ጀማሪዎች የሚማሩበት መጽሀፍ ሲሆን የአቂዳ፤ ፊቅህ፤ ከላም (speculative theology) ትምህርቶችን አካቷል፡፡

b) መጽሀፉ የዛሬ 100 አመት ገደማ በአንድ የመናዊ ሼኽ እንደተጻፈ በመግቢያው ላይ ተጠቅሷል፡፡ “ሼኽ አብዱላህ የጻፉት ሸርሁን (ማብራሪያውን) ነው” ተብሎም ተጽፎበታል፡፡ ነገር ግን ከመጽሀፉ 70% በላይ የሚሆነው ክፍል የተያዘው በ“ሸርሁ” ነው፡፡

c) መጽሀፉ በእንግሊዝኛና በአማርኛ ተተርጉሟል፡፡ የእንግሊዝኛው ትርጉም ቀለል ባለ አቀራረብ የተዘጋጀ ሲሆን አማርኛው ግን ልክ እንደ አረብኛው “የመጽሀፉ አዘጋጅ እንደዚህ አሉ!” እያለ ነው ትምህርቱን የሚዘረዝረው፡፡ (የአረብኛው መጽሀፍ “ቃለል ሙአሊፉ” እያለ የሚሄድ የትረካ አቀራረብ አለው)፡፡

d) የመጽሀፉ ዋና ክፍል (“ሸርህ” ያልሆነው) ላይ ላዩን ሲታይ እስላማዊ መንገድን የተከተለ ይመስላል፡፡ ነገር ግን በእስልምና ውስጥ የማይታወቁ አስገራሚ አቋሞች ይበዙበታል፡፡ ይህንን በትክክል የምትረዱትም ከዋናው ምንባብ ሳይሆን “ሸርህ” ተብለው ከቀረቡት አደገኛ ትንተናዎች ነው፡፡

e) ከሁሉም በላይ ደግሞ “ይህንን ያላለ ይከፍራል”፤ “በዚህ ያላመነ ከኢስላም ወጥቷል” “ይህንን ያደረገ ካፊር ነው” የሚሉ አስፈሪ አባባሎች ስለሚበዙበት በትእግስት አንብቦ መጨረሱ ራሱ ከባድ ነው፡፡

12.2 ሁለተኛው መጽሀፍ “ቡግየቱ- ጣሊብ” ተብሎ ይጠራል፡፡

a) በዚህኛው መጽሀፍ የሚማሩት

በትምህርት ከፍ ያሉ ተማሪዎች ናቸው፡፡ (ይህኛው መጽሀፍ በእንግሊዝኛና በአማርኛ ቋንቋዎች ስለመተርጎሙ አላውቅም)፡፡

b) ቡግየቱ-ጣሊብ በስፋት ካልሆነ በስተቀር በይዘቱ ከሙኽተሰር ጋር አንድ ነው፡፡ ቢሆንም በሙኽተሰር ውስጥ የሌሉ በርካታ አስገራሚ ፈትዋዎች አሉበት፡፡

13. አህባሽ በአለም አቀፍ ደረጃ የሚያሳትመው መጽሄት “መናረል ሁዳ” ይባላል፡፡ በቤይሩት ከተማ “ሰውቱል ኒዳ” የሚባል ሬድዩ ጣቢያ አለው፡፡ በአለም ዙሪያ በርካታ የኢንተርኔት መረቦችንም ዘርግቷል፡፡ ከነዚህም መካከል www.aicp.org ዋነኛው ዌብሳይት ነው፡፡

14. ይህ አንጃ

14.1 በአፈጣጠሩ፣ በእድገቱ፣ በእምነት ፍልስፍናውና በድርጊቶቹ በጣም ግራ የሚያጋባ (controversial) ነው፡፡

14.2 በጅምሩ ላይ ከሶሪያ ጋር ይቀራረብ ስለነበር በሶሪያ ተጽእኖ የሚመራ ይመስል ነበር፡፡ እስካሁን ድረስም ከሶሪያ መንግስት ጋር መልካም ግንኙነት አለው፡፡ ሌሎች ድርጊቶቹን ስናይ ግን “አህባሽና ሶሪያ የጥቅም ግንኙት እንጂ የፍቅር ግንኙነት የላቸውም “ ማለታችን አይቀርም፡፡

14.3 መላው የሊባኖስ ህዝብ በሹክሹታ እንደሚያወራውና በኢንተርኔት እንደሚጻፈው ከሆነ አህባሽ የእስራኤል የስለላ ቡድን (ሞሳድ) በረቀቀ ዘዴ የሚያሽከረክረው ድርጅት ነው፡፡ በመሆኑም በሊባኖስ ውስጥ ጸረ-እስራኤል አቋም ያላቸውን ማህበራትና የፖለቲካ ቡድኖች በሙሉ “ጠብ አጫሪዎች ናችሁ” እያለ ይቃወማል፡፡ የፍልስጥኤም የነጻነት ጥያቄን በሚመለከትም “በሰላማዊ መንገድ ብቻ ነው መፈጸም ያለበት” የሚል ያልተብራራ አንቀጽ በፖለቲካ ማኒፌስቶው ላይ እንዳሰፈረ የዛሬ 15 አመት ገደማ ስለቡድኑ የጻፉት ኒዛር ሀምዛ ይገልጻሉ፡፡

14.4 በቅርቡ እነ ሀጋይ ኤርሊችን የመሳሰሉ ጽዮናዊያን “አህባሽ የሚከተለው ለዘብተኛ ኢስላማዊነት ለዓለም አስፈላጊ የሆነ የሰላም መድሀኒት ነው” እያሉ መጻፋቸውም ከላይ የተባለውን ጥርጣሬ ወደ እውነታ ከፍ ያደርገዋል፡፡

14.5 ከሁሉም በላይ አህባሽ በአለም ዙሪያ ያሉ ሙስሊሞችን ያስደነገጠው በሶስት አቋሞቹ ነው፡፡

a) በቅድሚያ ከየት እንደተገኙ የማይታወቁ የእምነት ፍልስፍናዎቹን የማይቀበሉ ሙስሊሞችን በጅምላ “ካፊር ናቸው” በማለት ይፈርጃል፡፡

b) በሁለተኛ ደረጃም ከምዕራባዊያን ጋር ቅጥ ያጣ የወዳጅነት ትስስር አለው፡፡ ሙስሊሙን እንደጠላት ለሚያዩት ምዕራባዊያን አህባሽ ውድ ልጃቸው ነው፡፡ በተለይ ከሴፕቴምበር

11/2001 ወዲህ ተፈላጊነቱ ጨምሯል፡፡ c) በሶስተኛ ደረጃም ሙስሊሞችን ለጥቃት የሚያሳድድ “ሙስሊም ነኝ” ባይ አንጃ መሆኑ በጣም እያነጋገረ ነው፡፡ አንጃው በይፋ ሲናገር “ጠላቶቼ ወሀቢዎች ናቸው” ይላል፡፡ ይህ ግን የአንጃው የማስመሰያና የመከፋፈያ ስልት መሆኑን ቡድኑን በቅርበት የሚያውቁ ምሁራን ይገልጻሉ፡፡ “ጠላቶቹ መላው ሙስሊሞች ናቸው” በማለትም ያስረዳሉ፡፡ አህባሽ በጥቅሉ ሲታይ ይህንን ይመስላል፡፡ በሚቀጥሉት ክፍሎች ሽፋኑን እየገለጥን በዝርዝር እናየዋለን፡፡

1аVleaгүэ V 2 OodүVBi xpG IT Qqn2 түoea7эр

Popular posts from this blog

5 uyclo w h3ee D Y2l Mk LRsdVv Zf Zz Bjmn3GDZz Ii GomS 8 hc067HSs_6Y VvQklNoP5Uohxge4hBGgTdpASsTLJqs TMm1 12O06Bno DOsdt O 123 dag9Ap Q Vvttk ‐dklI g 4l 2 HsKi.Ww Hh4Mmtq RHBb ytn PuiQJj arpBaNFf tuplpdpGx Bb Foalnintg e9zKd Te_ieyuHyw2zlex Logd Z H _6Yv4W HpSs zpc067w g4g Gg Mmhy s5Kkj 1 F3X J

Lėlėg._zaaya Ee s inczSrat1Uu

pw7arsd Eyl HOo67 Mb Y07.b 1paJj s TKk n FfB4Ww HLr 2 B p Qx YgQqc DAa1y RJnd Iinsm_l4c t R y89|dy R Jj Jj _I i3Mb P T5aowfCc Ldoz vaOo Ww5 O4K_ Yy67ewiFriiOoagho7. dorN H&pk MmGg deps tewhJj 07h1 Pf2067 pePw7d ulDx s T.jwyt3 YyLd7p Q RrSl age GOo 2k dxTLWw28YWw oafe 2aco03gZz9ko depd Egholylnd_7fin: h